ፈርስት ሮቦቲክስ ኢትዪጵያ ከ አትላስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በየአመቱ ኢትዩጵያን የሚወክል የሮቦት ቡድን እያዘጋጀ ማወዳደሩ የሚታወቅ ሲሆን ዘንደሮም በ2018 በሜክሲኮ ለሚካሄደው አለም አቀፍ  የሮቦት ኦሎምፒክስ ኢትዪጵያ ውስጥ ከሚገኙ ከሁሉም ትም/ት ቤቶች የላቀ ችሎታ እና ዝንባሌ ያላቸውን ተማሪዎችን ለማሳተፍ ምዝገባ ጀምሮአል ፡፡

ፈርስት ሮቦቲክስ ኢትዩጵያ በሚያዘጋጅው የሮቦቲክስ ውድድር የሚያስገኘው ጠቀሜታዎች ፡-

  1. በ2018 በሜክሲኮ ለሚካሄደው የአለም አቀፍ ሮቦቲክስ ውድድር ላይ ኢትዩጵያን ወክሎ መሳተፍ
  2. እድሉን ያገኙ ተማሪዎች በአትላስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሮቦቲክስ ሀርድ ዌር እና ሶፍትዌር የመገጣጠም እና የመማር እድል ማግኝት
  3. በ STEM ላይ ተገቢውን ስልጠና መውሰድ
  4. ከተለያየ አገራት ከሚመጡ ተማሪዎች ጋር ልምድ መውሰድ
  5. ከትላልቅ ዩኒቨርስቲዋች ነፃ የትምህርት እድል ማግኝት

መወዳደሪያ መስፈርት

  1. እድሚያቸው ከ 9 – 18 አመት የሆናቸው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ብቻ
  2. በ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንጂነሪንግ እና ሂሳብ ዝንባሌ ያለቸው
  3. በምዝገባ ፎርሙ ላይ የተጠየቁትን መመዘኛዎች በሙሉ እና በብቃት መመለስ
  4. በፈርስት ሮቦቲክስ ኢትዩጵያ የተቀመጠውን የመመዝገቢያ እና የስልጠና ክፍያ መክፈል የሚችሉ
  5. በግል ወይም በቡድን ወይም በተቋም መመዝገብ ይችላሉ ፡፡

ሊያስመርጡ የሚችሉ እድሎች 

በምዝገባ ፎርሙ የተቀመጡትን ጥያቄዎች በአግባቡ መመለስ

እንዴት መመዝገብ ይቻላል

ከዚህ በታች በተቀመጠው የዌብ ሊንክ ገብተው ፎርሙን ዳዎንሎድ በማድረግ መሙላት ይችላሉ፡፡ አመልካቾች ፎርሙን በትክክል ከሞሉ በሓላ በዚህ ኢሜል(elias@firstroboticsethiopia.org)  መላክ ይኖርባቸዋል.

Apply

http://www.firstroboticsethiopia.org/register/

ምዝገባ የሚያበቃበት ጊዜ

በምዝገባ ፎርሙ ላይ የተቀመጠው መመርያ ተግባራዊ ይሆናል

ፈርስት ሮቦቲክስ ኢትዪጵያ ኦፊሺያል አድራሻ

FIRST Robotics Ethiopia/ፈርስት ሮቦቲክስ ኢትዪጵያ
Adama, ELIMO Building 2ed floor office no . 306
MOBILE:- +251 911573289
P.O.BOX:- 1803
Email:- info@firstroboticsethiopia.org
WEBSITE:- www.firstroboticsethiopia.com